የፊሊጶስ አደፍርስ ፋውንዴሽን ዓላማ እና ግብ

የፋውንዴሽኑ አላማ የቅርብ ዘመዶቻቸውን በሞት ላጡ ቤተሰቦች በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መደገፍ ነው። ይህንንም ለማሳካት በኢትዮጵያ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና የእግር ኳስ አካዳሚዎችን ማቋቋም እንዲሁም ከዚህ ዓላማ ጋር የተያያዙ ተግባራትን ማስተዋወቅን ይጨምራል። ፋውንዴሽኑ በዋናነት የሚንቀሳቀስው በስዊድን እና በኢትዮጵያ ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፥

  • በሀዘን ለተጎዱ ቤተሰቦች የመነጋገሪያ መድረክ ማሰናዳት፣ የልምድ ልውውጦች እንዲያካሄዱ መርዳት፣ የውይይት መድረኮችን እና ድጋፍን ማምቻችት።
  • በኢትዮጵያ ያሉ የወጣት ቡድኖችን ለማጠናከር እና ለመደገፍ የእግር ኳስ እና የተለያዩ የስፓርት ትጥቆችን ማሰባሰብ።
  • የእግር ኳስ አካዳሚ ቡድኖች እንዲያድጉ እና እንዲበረታቱ የሚረዳቸውን የገንዘብ ድጋፍ ማሰባሰብ።
  • ትምህርትን ማበረታታትና የትምህርት ቁሳቁሶች አቅርቦት ማሰባሰብ፣ ትምህርት ቤቶችንና የአብነት ተማሪዎችን መረዳት ለእነሱም የሚሆነውን የገንዘብ ድጋፍ ማሰባስብ፣ ትምህርት ተቋማትን መገንባት እና ማደሰ ፣ የትምህርትና የጤና እንክብካቤ ፕሮግራሞችን በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ከባለሙያዎች ጋር በመተባበር ስልጠና መስጠት።

የፋውንዴሽኑ ቦርድ ንብረቶች በሚገባ ተጠበቀው እንዲተዳደሩና ተገቢውን ያህል ትርፍ ማምጣት እንዲችሉ ሆኖ መሰራት አለበት። ከምስረታው እና በድረ-ገፅ ላይ ከወጣ በኋላ የሚገቡት ማንኛውም ንብረቶች እና ገንዘቦች የሚውሉት የፋውንዴሽኑ ዓላማ እና ግብ ላይ ይሆናል። ፋውንዴሽኑም ከላይ የተቀመጡ ዘላቂ አላማዎችን የሚያራምድ ራሱን የቻለ ሃብት መፍጠር አለበት።

ፋውንዴሽኑ የተሰበሰበውን ገንዘብ በመጠቀም ህጋዊ አካላትን በማመልከቻ ሂደት በማስተናገድ የፋውንዴሽኑን ዓላማ በሚያሳኩ መንገዶች ላይ የሚሰሩትን በመደገፍ ዓላማውን ለማሳካት ይጥራል። የፋውንዴሽኑ ቦርድ አስተዳዳሪ የተሰበሰበውን ሃብት ያስተዳድራል።

እርዳታ ለመስጠት

በ Swish – 070 – 750 40 54   ወይም
በ  Gofundme Link.

በኩል ስጦታ መለገስ ይችላሉ። ሲለግሱ ለፊሊጶስ አደፍርስ ፋውንዴሽን ብለው ይፃፉ። 

Vila i frid
Länge leve FillE